አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ አበባ ተመዝግበው ሰሌዳ እየተጠባበቁ ባሉ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል
ይህ የአዲሱ ተሽከርካሪ ሰሌዳ ETH የሚል አለምአቀፋዊ ኮድ የያዘ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የአተገባበር ሂደቱ በአዲስ አበባ መጀመሩ ተገልፆል።
የታርጋ ዋጋዉን በተመለከተ የወጣ ስትራቴጂ ያለ መሆኑን እና ህዝብ በብዛት የሚጠቀማቸው የብዙሃን ትራንስፓርት እና የግል ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ዋጋዉ ላይ ልዩነት እንደሚኖር ሰምተናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን የአዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ይዘት÷ አተገባበር እና አስፈላጊነት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ባለስልጣኑ በመግለጫዉ በመዲናይቱ አሁን ላይ ተመዝግበው ሰሌዳ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ተገልፆል።
የመጀመሪያዉ ሰሌዳ ባለስልጣኑ ካሉት 11 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች አንዱ በሆነዉ የየካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መሰጠቱ ተነግሯል።
መግለጫዉን የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘገየ በላይነህ እንደገለፁት አዲሱ የሰሌዳ ሀገራዊ ይዘት ያለዉ እንዲሁም ሰሌዳዉ ፎርጂድ አይሰራም ብለን እናምናለን ሲሉ ገልፀዋል።
አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለህግ ማስከበር የሚመች እና ምን አይነት ተሽከርካሪ እና የተሽከርካሪ ባለቤት ማነዉ የሚል ማሳያዎችን ይዟል ተብሏል።
የረዥም ጊዜ የሚያገለግል እና የሀብት ብክነት የሚቀንስ መሆኑ አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሰሌዳ ብቻ የሚጠቀም የሚያደርግ ነዉ ሲል ባለስልጣኑ በመግለጫው ተነግሯል።
አዲሱ ሰሌዳ ተሽከርካሪዉ እስኪወገድ ድረስ የሚያገለግል ይሆናል ያለዉ ባለስልጣኑ ከ800 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች አሉ ሰሌዳዉ ተወስዶ መች ይጠናቀቃል በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።
በሁሉም ተሽከርካሪዎች አዲሱን ሰሌዳ ተግባራዊ ለማድረግ በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በሚያስቀምጣቸው የጊዜ እቅድ ሰሌዳዉን የመቀየር ሂደቱ እንደሚተገበር ነዉ የተገለፀው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን 1050/2017 መመሪያን በዛሬዉ እለት መተግበር መጀመሩን አሳዉቋል።
ቁምነገር አየለ

3 days ago