Logo
Getu Temesgen
በ5ኛ ዙር የሀጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት 11 ዘርፎች ለዓመቱ ምርጥ ሽልማት ይቀርባሉ
#ethiopia | ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን 6ተኛውን የሀጫሉ መታሰቢያ እና 5ኛውን የሀጫሉ ሽልማት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ይህ ሽልማት በየአመቱ የሚዘጋጀው አርቲስቱን እና ስራዎቹን ለማስታወስ እንዲሁም ለመዘከር መሆኑም ተጠቁሟል።

በዘንድሮው የሽልማት መርሃ ግብርም ከሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሕዝብ የቀረቡ የአንድ ዓመት ስራዎች በውድድሩ ይካተታሉ ተብሏል።

አልበሞችን ጨምሮ 250 ያህል ስራዎች በኮሚቴዎች እንደሚሰበሰቡ የተገለፀ ሲሆን፤ ለዚሁ ሽልማት በተቋቋሙ 32 ዳኞች እንደሚለዩ ተገልጿል።

90 በመቶው በዳኞች እና በባለሙያ ነጥብ ሲሰጥ ፣ ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ በህዝብ ምርጫ የሚሰጥ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።

11 ዘርፎች ለዓመቱ ምርጥ የሽልማት ዘርፍ እንደሚቀርቡ የተገለጸ ሲሆን ፣ በህዝብ ድምፅ የሚሰጥባቸው እና በተዘጋጀው ዌብሳይት የሚወጡት 6 ዘርፎች ናቸው ተብሏል።

ማህበረሰቡም ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚፈልጉትን ባለሙያ እና ስራዎች መምረጥ እንደሚችሉ በመግለጫው ተጠቁሟል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ በየዓመቱ ሰኔ 22 ቀን ይካሄዳል።

ዘገባው የAMN ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.