Logo
SeledaPost
አንድ ካፒቴን ያለ ትክክለኛ ፈቃድ ለ17 ዓመታት ኤር ካናዳን ሲያበር መቆየቱ ተደረሰበት!
 
በአቪዬሽን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አስገራሚ ማጭበርበር በካናዳ ተጋለጠ። ጄፍሪ ዎል የተባለ የቀድሞ የኤር ካናዳ (Air Canada) ፓይለት፣ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም እና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣል በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል። ይህ ፓይለት ምንም እንኳን የንግድ አውሮፕላን የማሽከርከር መሰረታዊ ፈቃድ የነበረው ቢሆንም፣ እንደ ቦይንግ 777 እና 787 ያሉ ግዙፍ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን በካፒቴንነት ለመምራት የሚያስችለውን አስገዳጅ የበረራ ትራንስፖርት ፓይለት ፈቃድ ሳይኖረው ነው ለረጅም ዓመታት ሲሰራ የቆየው።
 
ማጭበርበሩ የተፈጸመው ከ2009 እስከ 2025 ባሉት 17 ዓመታት ውስጥ ሲሆን፣ ግለሰቡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ900 በላይ ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ በረራዎችን በዋና አዛዥነት መርቷል። ይህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን ህይወት ለአደጋ ያጋለጠ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል።
 
ጉዱ የወጣው በቶሮንቶ ፒየርሰን አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ ድንገተኛ የሰነድ ፍተሻ ሲሆን፣ አየር መንገዱ ወዲያውኑ ከስራ አግዶታል። ኤር ካናዳ መንገደኞቹ በቴክኒክ ደረጃ አደጋ ላይ እንዳልነበሩና ፓይለቱ በየስድስት ወሩ የሚሰጠውን የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ስልጠና ያልፍ እንደነበር ቢገልጽም፣ የካናዳ ፖሊስ ግን ጉዳዩን እንደ ከባድ የወንጀል ድርጊት በመቁጠር ከፍተኛ ምርመራ እያደረገበት እንደሚገኝ ተመላክቷል።
 
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.