Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘለንስኪ በ‹‹ፍላሚንጎ›› ሚሳኤል ሩሲያ ውስጥ ዘልቀው ገብተው ጥቃት ማድረሳቸውን አስታወቁ፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በምስራቃዊ ሞስኮ በሚገኝ አንድ ወታደራዊ ፋብሪካ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገለፁ፡፡ ፕሬዝደንቱ እንዳሉት ይህ ጥቃት የተፈፀመው ዩክሬይን በአገር ውስጥ በሰራችው ሚሳኤል ነው፡፡

ሲናገሩም ‹‹ለሊቱን ዩክሬይን ሰራሽ በሆነው ኤፍፒ 5 ፍላሚንጎ ሚሳኤል በቼቦስካሪ ከተማ ያለ ወታደራዊ ፋብሪካ ላይ ጥቃት አድርሰናል፡፡ ይህ ፋብሪካ ለሩሲያ መከላከያ ሀይል የድሮንና ሚሳኤል መለዋወጫዎችን የሚያመርት ነው›› ብለዋል፡፡ አያይዘውም ወደዚህ ፋብሪካ አንድ ሚሳኤል ሲወነጨፍ የሚያሳይና የቃጠሎ ምስሎችን አቅርበዋል፡፡ ቼቦስካሪ ከተማ ከዩክሬይን ድንበር በ1000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህንን ጥቃት የአካባቢው ባለስልጣናት አረጋግጠው የደረሰውን ጉዳት እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.