የመጨረሻ የዓለም ዋንጫቸውን የሚያደርጉ ከዋክብት…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለምን ቀልብ የሚይዘው ትልቁ የእግር ኳስ መድረክ የዓለም ዋንጫ ውድድር ሊጀመር ነው።
እግር ኳስ፣ ህብረ ዜማ እና በቀለማት ያሸበረቁ በስሜት ጫፍ የከነፉ ደጋፊዎች ፈንጠዝያ ምድሪቱን ሊነቀንቋት ቋምጠዋል።
ከተኩስ ድምጽ ወደ ደጋፊ የሀሴት ዜማ የዓለም የትኩረት አይኖች ይታጠፋሉ፤ ምክንያቱም ይህ መድረክ ሰላማዊ ጦርነት ነው፡፡
ታድያ ኮከቦች የክብር ማማ ላይ ለመውጣት የሚያደርጉት ፍልሚያ እንደመሆኑ የትውልድ ቅብብሎሽና ለሀገራዊ ክብር የሚከፍሉት መስዋዕትነት ውድድሩን በየአራት ዓመቱ የጉጉት ምንጭ አድርጎታል።
እግር ኳስ በቡድን የሚጫወቱት ቢሆንም፣ የዓለም ዋንጫን ግን ሁልጊዜም ልዩ የሚያደርጉትና ሚሊዮኖችን አይን እና ጆሮ ቀልብን የሚሰቅዙት የሜዳ ላይ ኮከቦች ግላዊ ታሪክ፣ ስሜት እና አስደናቂ ክህሎት ናቸው።
የእግር ኳስን ታሪክ ለሁለት አስርት ዓመታት በበላይነት የገዙት ኮከቦች የመጨረሻ ምዕራፋቸውን የሚፅፉበት መሆኑ ውድድሩ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡
በኳታር የዓለም ዋንጫ የነገሰው ሊዮኔል ሜሲ በአርጀንቲና ማሊያ በድጋሚ ታሪክ ለመጻፍ አሻራውን ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቀመጥ ወደ ሜዳ ይገባል።
እድሜን ቁጥር ያደረገው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የመጨረሻ የዓለም ዋንጫ ውድድሩን ያደርጋል፡፡
ለሀገሩ የመጨረሻውን የክብር ስጦታ ለማበርከት የሚያደርገው ተጋድሎ ውድድሩን ከፍ ያደርገዋል፡፡
የዓለም ዋንጫው ደግሞ በሌላ ገጽታው የአዲሱ ትውልድ ንጉሦች ፍልሚያን ያስመለክተናል።
ከእነሱ በተጨማሪ ክሮሺያዊው ኮከብ ሉካ ሞድሪች እና ኔይማር ጁኒየር የመጨረሻ የዓለም ዋንጫ ውድድራቸውን ያደርጋሉ፡፡
ሜሲ፣ ሮናልዶ እና ኔይማር የመጨረሻ የዓለም ዋንጫቸው ላይ የአሸናፊነት ደስታ ወይም በእንባ የታጀበ ስንብትን ሊያስመለክቱን ውድድሩ ሊጀመር ነው።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

5 days ago