(ዘ-ሐበሻ ዜና) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ የጥበቃ በረራ እያደረገች የነበረችን የአሜሪካ አፓቺ ሄሊኮፕተር መትታ ጥላለች በማለት ከሰዋል። ፕሬዝዳንቱ ማክሰኞ ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለዚህ ጥቃት ተገቢውን የአጸፋ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቀዋል።
ትራምፕ በ"ትሩዝ ሶሻል" ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ በጥቃቱ ወቅት በሄሊኮፕተሯ ውስጥ የነበሩት ሁለቱ አብራሪዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑንና ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። አክለውም "ምንም እንኳን አብራሪዎቹ በህይወት ቢኖሩም፣ ዩናይትድ ስቴትስ የግድ ለዚህ ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት አለባት" ሲሉ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።
በሌላ በኩል የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ትናንት ምሽት በኦማን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ኤኤች-64 (AH-64) የተሰኘችው አፓቺ ሄሊኮፕተር መውደቋን ያረጋገጠ ቢሆንም፣ ለክስተቱ ኢራንን በቀጥታ ተጠያቂ ከማድረግ ተቆጥቧል። ማዕከላዊ እዙ ባወጣው መግለጫ የሄሊኮፕተሯ የመከስከስ መንስኤ በምርመራ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
በአደጋው ውስጥ የነበሩት ሁለቱ ወታደሮች አደጋው ከደረሰ ከሁለት ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በአሜሪካ የባህር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ እና በ82ኛው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር የጋራ ጥረት ከሞት መትረፍ መቻላቸውን የዕዙ መግለጫ አክሎ አስረድቷል።

5 days ago