Logo
FBC

እየተጠናቀቀ የሚገኘው ዞብል ፓርክ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ታሪካዊ ከተማ ልዕልና የሚለካው በትናንትናው ገድል ብቻ ሳይሆን ዛሬ መሬት ላይ በሚታተሙ ሕያውና ጽኑ የልማት ማኅተሞች ነው አሉ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው።

ከንቲባው ፓርኩን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ጎንደር ሙሽራነቷንና እውነተኛ ውበቷን ከፍ አድርገው ከሚያሳዩ የኮሪደር ልማቶች መካከል አንዱ የዞብል ፓርክ ነው።

በ5 ነጥብ 1 ሄክታር መሬት ላይ ፍጹም በረቀቀ ጥበብ ያረፈውና በአሁኑ ሰዓት የኮንስትራክሽን ሥራው እየተጠናቀቀ የሚገኘው ፓርኩ÷ ተራ የድንጋይና የሕንፃ ክምችት አለመሆኑን ተናግረዋል።

ልማቱ ማኅበረሰቡ በቅንነትና በባለቤትነት ሲሳተፍበት ውጤቱ ምን ያህል ውብ፣ ያማረና የማይበገር መሆኑን በአደባባይ የመሰከረ የከተማችን ጽኑ የልማት ገጽታ ነው ብለዋል፡፡
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.