Logo
SeledaPost
ትራምፕ እስራኤል ጥቃት እንዳትፈፅም ቢያስጠነቅቁም በኢራን ላይ ድብደባ ፈፀመች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከተጨማሪ ጥቃቶች እንዲቆጠቡ ከተናገሩ በኋላም እስራኤል ሰኞ እለት ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቷን አስታውቋለች።ከሰአታት በፊት ትራምፕ በእስራኤል እና በኢራን የሚደረጉ አዳዲስ ጥቃቶች አስተዳደራቸው ከቴህራን ጋር በሚያደርገው የሰላም ድርድር ላይ ተጽእኖ እንደማይኖረው በመግለጽ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጥቃት እንዳይፈፅሙ ጠይቀው ነበር።

የእስራኤል ጦር ከሚያዝያ ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢራን ለተፈፀመበት ጥቃት አፀፋውን እንደሚመልስ በማስጠንቀቅ በምእራብ እና በማዕከላዊ ኢራን በሚገኙ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል የእስራኤል አቻቸው ለኢራን ጥቃት አጸፋ እንዳይሰጡ ማሳሰባቸውን በርካታ የዜና አውታሮች ዘግበዋል።

እስራኤል የአየር ሀይሉ በማዕከላዊ እና በምእራብ ኢራን ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቱን ከተናገረ በኋላ የኢራን መንግስት ቲቪ በዚህ ሰዓት በሶስት ከተሞች ፍንዳታ እየደረሰ መሆኑን እየዘገበ ይገኛል። የመንግስት ቲቪ በቴሌግራም ላይ ባሰራጨው ዘገባ "በቴህራን፣ ታብሪዝ እና ኢስፋሃን በርካታ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። በማዕከላዊ ካራጅ አቅራቢያ ፍንዳታዎችም ተሰምተዋል ተብሏል።

የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ (IRGC) በሰሜን እስራኤል ላይ የተተኮሱ በርካታ የሚሳኤሎች ማዕበል “የአንድ ሳምንት ሙሉ ተከታታይ ጥቃቶች መጀመሪያ ናቸው” ብሏል። በእስራኤል ላይ ያነጣጠሩ አብዛኞቹ ሚሳኤሎች የተጠለፉ መሆናቸው የተሰማ ሲሆን እስራኤላውያን አሁን መጠለያቸውን መልቀቅ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል።
Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.