Logo
Getu Temesgen
ወጣቱ ሰኢድ ታቦር ከቅርጫት ኳስ ተጫዋችነት ተነስቶ ዓለም አቀፍ ዳኛ መሆን የሚያስችለውን ብቃት አረጋገጠ
#ethiopia |
የወልቂጤ ከተማ ፍሬ የሆነው ወጣቱ ሰኢድ ታቦር በሀገሪቱ የቅርጫት ኳስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ አዲስና ተስፋ ሰጪ ምዕራፍ አስመዝግቧል።

በትጋቱና በማይበገረው ጥንካሬው ከሜዳ ተጫዋችነት ተነስቶ ዛሬ የዓለም አቀፍ የቅርጫት ኳስ ዳኝነት ደረጃ ላይ መድረስ ችሏል።

በወልቂጤ ከተማ የቅርጫት ኳስ ክለብ ውስጥ ከታችኛው ፕሮጀክት ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት በተጫዋችነት ካገለገለ በኋላ፣ ለተተኪ ወጣቶች ዕድል ለመስጠት ወደ ዳኝነቱ ዓለም በመግባት ውጤታማ መሆን የቻለ አርአያ የሚሆን ወጣት ነው።

ወጣቱ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሰኢድ ታቦር ላለፉት ሁለት ወራት በዓለም አቀፍ የቅርጫት ኳስ የሰንጠረዥ ዳኝነት ስልጠና ላይ በንቃት ሲሳተፍ የቆየ ሲሆን፣ የተጠየቁትን ጥብቅ መስፈርቶች በሙሉ በብቃት በማጠናቀቅ የዓለም አቀፍ ዳኝነት ፈቃዱን በይፋ ተቀብሏል።

ከጉልበት ሥራ ተነስቶ እስከ ስኬት ማማ የደረሰበት የሰኢድ የሕይወት ጉዞ ቀላል አልነበረም። ከዳኝነት ፉጨቱ በጀርባ በርካታ የማይታዩ ልፋቶች፣ የቀንና የሌሊት ጥረቶች፣ እንዲሁም ለስፖርቱ ያለው ከፍተኛ ፍቅርና ታማኝነት ይገኛል።

ወልቂጤ ያፈራችው ይህ ብሩህ ኮከብ፣ ለሀገራችን ወጣቶች በሙሉ በትጋት ለሚሠራ ሰው የማይደረስበት የላቀ ስኬት እንደሌለ ትልቅ ማሳያና አርዓያ ሆኗል።

መላው የስፖርቱ ቤተሰብ በዚህ ታሪካዊ ስኬት ታላቅ ኩራት የተሰማው ሲሆን፣ ለወጣቱ ዳኛም መልካም ምኞቱን ገልጾለታል።

ኑሬ ረጋሳ
ከወልቂጤ
#ethiopianbasketball #internationalreferee #wolkiteyouth #ethiopiansport #basketballreferee #inspirationaljourney #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.