(ዘ-ሐበሻ ዜና) "የፕሬዝደንት ዘለንስኪ ደብዳቤ ደርሶናል" ስትል ሩሲያ አስታወቀች፡፡ የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ የፃፉት ግልፅ ደብዳቤ እንደደረሳት ሩሲያ ይፋ አደረገች፡፡ የሩሲያ ቤተመንግስት የሆነው ክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዛሬ በፒትስበርግ እየተከናወነ ባለው አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ በሰጡት ቃለምልልስ ‹‹ዘለንስኪ የፃፉትን ደብዳቤ በተመለከተ የሰማነው ትላንት ነበር፡፡
ይህንንም ለፕሬዝደንት ፑቲን እንዲደርሳቸው አድርገናል›› ብለዋል፡፡ በደብዳቤው ላይ ፕሬዝደንት ፑቲን ምን አስተያየት እንደሰጡ ተጠይቀው ሲመልሱ ግን ‹‹በዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ መሄድ አልፈልግም›› በማለት ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ትላንት በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል ውይይት በቀጥታ ከሩሲያው አቻቸው ጋር ማድረግ እንደሚፈልጉ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
በደብዳቤያቸው ከፑቲን ጋር ገለልተኛ በሆነ አገር ለምሳሌ በስዊዘርላንድ፣ በቱርክ ወይንም በአረብ አገራት ውስጥ ፊት ለፊት በመገናኘት ፍላጎት እንዳላቸው የጠቀሱ ሲሆን ውይይቱም ከተኩስ ማቆም አንስቶ እስከ ምርኮኛ መለዋወጥ ድረስ ቢሆን ደስ እንደሚላቸው አስታውቀው ነበር፡፡

2 months ago