Logo
SeledaPost
ሕወሃት አዲስ አውዳሚ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ ጥሪ አቀረበ።

ህውሃት ከፊታችን አውዳሚ ጦርነት እየመጣ ይገኛል አስወግዱ ሲል ለአለማቀፍ ማህብረሰብ ባሰራጨው ደብዳቤ፣ በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል ገልጿል።

በምርጫ ቦርድ እውቅናው የተሰረዘው ድርጅቱ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም "ሊቀረፍ የማይችልና አውዳሚ ጦርነትን ለመከላከል የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ" በሚል ርዕስ ለዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች እና ለዓለም አቀፍ አጋሮች ባሰራጨው የዲፕሎማሲያዊ ማስታወሻ ሀገሪቱ ወደ አዲስ የትጥቅ ግጭት እያመራች መሆኑን አስጠንቅቋል።

እንደ ሕወሃት መግለጫ ከሆነ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የውይይት እና የስምምነት መንፈስ እየጠፋ በመምጣቱ በእርሱ ፋንታ "የአንድ ወገን ውሳኔ፣ ማስገደድ እና ወታደራዊ የኃይል እርምጃ" ፖሊሲዎች እየነገሱ መጥተዋል ብሏል። ይህ አካሄድ መቀጠሉ ደግሞ ዳግም የትጥቅ ግጭት መከሰቱ የማይቀሬ እንዲሆን እያደረገው ነው ብሏል።

ይህ ሊቀሰቀስ የሚችለው ጦርነት በኢትዮጵያ ድንበር ብቻ ተወስኖ እንደማይቀር የጠቆመው መግለጫው በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ቀጣናዊ ውጥረት እና ለጎረቤት ሀገራት የሚታየውን የጠብ አጫሪነት ዝንባሌ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ግጭቱ አጠቃላይ ቀጣናውን ሊያናጋና ሰብዓዊ ቀውሱን ሊያባብስ እንደሚችል አመልክቷል።

የፌዴራል መንግሥቱ "ግትር አቋም" ይዟል ሲል የወቀሰው ሕወሃት፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ግን አሁንም ለሰላማዊ መፍትሔ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።

ከሰሞኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትግራይ ወጣቶች ወደ ወታደራዊ የስልጠና ካምፖች መግባታቸውን ሪፖርቶች በተሰሙበት በዚህ ወቅት የወጣው መግለጫ ጨምሮም "ማንኛውም ማህበረሰብ ሊሸከመው የሚችለው የጽናት ገደብ አለው" በሚል በትግራይ ላይ ያለው ጫና መጥበቁን የገለጸው ድርጅቱ፣ ቢሆንም ግን ብቸኛው አማራጭ መንገድ የፖለቲካ ውይይት መሆኑን በጽኑ እንደሚያምን አስታውቋል።

በመጨረሻም ሕወሃት የችግሩን ስር የሰደዱ መንስኤዎች ለመፍታት እንዲቻል፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚመራና የሚደገፍ ታማኝ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመርና ለዚህም ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው ገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.