(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሪፐብሊካን ፓርቲው የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ቶማስ ማሲ መንግስታቸው ለእስራኤል እያደረገ ያለውን የገንዘብ ድጋፍ አጥብቀው የተቹ ሲሆን፣ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መካከል ተፈጥሯል የተባለውን የከረረ የቃላት ልውውጥ "ባዶ ወሬ ነው" ሲሉ አጣጥለውታል።
ህግ አውጭው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ "ሁሉ ነገር ወሬ ነው። ለእስራኤል የሚሰጠውን የውጭ እርዳታ ለአንድ ወር ብቻ ብታቋርጡት ጎረቤቶቻቸውን በቦምብ መደብደብ ያቆማሉ። ያኔ ፈጣን ሰላም ይመጣል፣ የሆርሙዝ ስትሬት (የባህር በር) ክፍት ይሆናል፣ እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ በአንድ ጋሎን 2 ዶላር ይቀንሳል" ብለዋል።
አክለውም "እስራኤል ከአሜሪካ ግብር ከፋዮች ከፍተኛውን የእርዳታ ገንዘብ የምትቀበል ሀገር ሆና ቆይታለች፤ አሁንም ያንኑ በመቀጠል ላይ ትገኛለች" ሲሉ የሀገራቸውን የውጭ ፖሊሲ አጥብቀው ተችተዋል።

2 months ago