Logo
SeledaPost
⚡ "ግብፅ ወደ ባህር በር እንዳንደርስ እያገደችን ነው" — ኢትዮጵያ

​ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ግብፅ ለማደናቀፍ እየሞከረች ነው ስትል በይፋ ከሰሰች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ የግብፅን አካሄድ "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ ኮንነዋል።

​📌 ግብፅ በቅርቡ ከኤርትራ፣ ከሶማሊያ እና ከሱዳን ጋር ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶችን በማድረግ ኢትዮጵያን የመክበብ ስትራቴጂ እየተከተለች እንደሆነ ይነገራል። የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "የቀይ ባህር ጉዳይ የሚመለከተው የባህር ጠረፍ ያላቸውን ሀገራት ብቻ ነው" ማለታቸው፣ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲ የማግለል ሙከራ ተደርጎ ተወስዷል።

​ አለመግባባቱ ከህዳሴው ግድብ ውጥረት ጋር የተያያዘ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የጀመረችውን ጨምሮ የባህር በር ባለቤት የመሆን ፍላጎቷን በሰላማዊ መንገድ እንደምትቀጥል አስታውቃለች

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.