Logo
Getu Temesgen
በደቡባዊ ጣሊያን የባህር ዳርቻ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
#ethiopia | በዛሬው ዕለት በማለዳው ክፍለ ጊዜ በደቡባዊ ጣሊያን የባህር ዳርቻ አካባቢ በሬክተር ስኬል መለኪያ 6 ነጥብ 1 የደረሰ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ማጋጠሙ ተገልጿል።

የጀርመን የጂኦሳይንስ ምርምር ማዕከል ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ይህ የተፈጥሮ አደጋ የተከሰተው ከምድር ወለል በታች 253 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ ነው።

አደጋው በተለይ ማክሰኞ ሌሊት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ንጋት ላይ የተመዘገበ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃዎች እየተሰበሰቡ ይገኛሉ።
#italy #earthquake #seismic #worldnews #europe #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.