Logo
Getu Temesgen
የዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) እናት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በበጀትና ሂሳብ ባለሙያነት ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ተድላ በ74 ዓመታቸው አርፈዋል።

የሽኝት እና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ እንደሚፈጸም ታውቋል።

ባለፈው ወር በዩናይትድ ስቴትስ 74ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት ወይዘሮ ቅድስት አምስት ልጆቻቸውን በጥሩ ሥነ ምግባርና በትጋት ያሳደጉ ጠንካራ እናት ነበሩ።

የታዋቂዋ ዘማሪ ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) እንዲሁም የዶክተር ለዓለም ጥላሁን፣ የጂጂ ጥላሁን፣ የኪኪ ጥላሁን እና የዳግማዊ ጥላሁን እናት የሆኑት ወይዘሮ ቅድስት ጳውሎስ ላለፉት 13 ዓመታት መኖሪያቸውን በአሜሪካ አድርገው ቆይተዋል።

ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው በሙሉ በውጭ ሀገር የሚኖሩ በመሆኑ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እሮብ ዕለት በሜሪላንድ እንደሚፈጸም ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የሟች ሙሉ የሕይወት ታሪክ በቅርቡ በተወዳጅ ሚዲያ ዲጂታል አማራጮች የሚቀርብ ሲሆን ለተባረከው ቤተሰብ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
#ሊሊ_ጥላሁን #ቃልኪዳን_ጥላሁን #የቀብር_ሥነ_ሥርዓት #ሀዘን #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.