Logo
SeledaPost
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ኢቶሪካ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም መውጣቱን ተከትሎ የቅርብ ጓደኛው አቶ ዩሱፍ ያሲንን ጨምሮ የታሰሩት ስምንት ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስትና እንዲለቀቁ እንደተወሰነላቸው ተሰማ።

ከአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን ጋር ቅርብ የሥራ ግንኙነት ያላቸው  ምንጭ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ታሳሪዎቹ እንዲለቀቁ የወሰነዉ ትናንት ነዉ። እነዚህ ታሳሪዎች በየግል አንድ፤ ሁለት እንዲሁም ሦስት ክሶች እንደቀረቡባቸው ነው የመረጃ ምንጩ የተናገሩት።

አዲስ የሙዚቃ ሥራዎቹ በዩትዩብ መድረክ ማስታወቂያ እንዲታጀቡ አስፈላጊ ሂደቶችን ለማመቻቸት ጀምራ ከነበረው ወይዘሮ ማኅሌት ሰለሞን(በትክክለኛ ስሟ ሃና ሰለሞን) እና አቶ ዩሱፍ ያሲን እያንዳንዳቸው የመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲከፍሉ ታዝዘው በትናንትናው ዕለት ከፍለው ማጠናቀቃቸውንም አስረድተዋል።

  በተለምዶ ሲኤምሲ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ቴዎድሮስ ስቱዲዮ ሁለት ጠባቂዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው 50 ሺህ ዋስትና እንዲያስይዙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብለዋል።

ጠባቂዎቹ ዋስትና ለመክፈል በሂደት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል። የዋስትና ከፍለው ያጠናቀቁት ሁለቱ ታሳሪዎች እስካሁን ከእስር እንዳልወጡ ሆኖም ግን እስከ ሰኞ ይወጣሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። 

[ዶይቸ ቬለ]

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.