Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት ዜና) — በሊጉ የደረጃ ማጣሪያ (Play-offs) ጨዋታዎች ወቅት በሦስት ክለቦች ላይ የቪዲዮ የስለላ ወንጀል መፈጸሙን ማመኑን ተከትሎ፣ ሳውዝሃምፕተን ከውድድሩ ውጭ እንዲሆን ተወሰነ። በግማሽ ፍጻሜው በሳውዝሃምፕተን ተሸንፎ የነበረው ሚድልስብሮ በምትኩ ወደ ውድድሩ የተመለሰ ሲሆን፣ ቅዳሜ ዕለት በዌምብሊ ስታዲየም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ከሃል ሲቲ ጋር ይጫወታል።

የእንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ እንዳስታወቀው፣ ሳውዝሃምፕተን በኦክስፎርድ ዩናይትድ፣ ኢፕስዊች ታውን እና ሚድልስብሮ የልምምድ ሜዳዎች ላይ ያለፈቃድ በድብቅ የቪዲዮ ቅረጻ ሲያካሂድ ነበር። ይህንን ተከትሎ ክለቡ ከዘንድሮው የዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ከመደረጉም በላይ፣ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን የ4 ነጥብ ቅናሽ ተጥሎበታል።

በዚህ ውሳኔ ሳውዝሃምፕተን ቢያንስ 110 ሚሊዮን ፓውንድ የቴሌቪዥን ስርጭት ገቢ የሚያስገኘውንና በአለማችን ውዱ ጨዋታ ተብሎ የሚጠራውን የፋይናል ፍልሚያ ያጣ ሲሆን፣ ክለቡ የተጣለበት ቅጣት ካለው ጥፋት አንጻር የማይመጣጠን በመሆኑ ረቡዕ ዕለት ይግባኝ ለማለት መዘጋጀቱ ታውቋል።

26 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.