አ-ር-ሰ-ና-ል!
#ethiopia | አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለመጨበጥ የሚያደርገውን ጉዞ ያቀና መቶ በመቶ ስኬታማ ድል አስመዘገበ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መድፈኞቹ ከበርንሌይ ጋር ያደረጉትን ተጠባቂ ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ወደ ካዝናቸው ከትተዋል።
ለለንደኑ ክለብ ብቸኛዋን የድል ግብ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ማጥመድ የቻለው ጀርመናዊው ኮከብ ካይ ሃቨርትዝ ነው።
ይህን ውጤት ተከትሎ አርሰናል አጠቃላይ የነጥብ ክምችቱን ወደ 82 ማድረስ የቻለ ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ተቀናቃኙ ማንቸስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 አሳድጓል።
ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ ከቦርንማውዝ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ነጥብ የሚጥል ከሆነ መድፈኞቹ የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ የሻምፒዮንነት አክሊል በይፋ የሚቀዳጁ ይሆናል።
#arsenal #burnley #epl #football #soccer #premierleague #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago