Logo
Getu Temesgen
ሲመስ ኮልማን ጫማውን እንደሚሰቅል ተነገረ
#ethiopia | አንጋፋው የኤቨርተን የቀኝ መስመር ተከላካይ ሲመስ ኮልማን በያዝነው የውድድር አመት መጨረሻ ጫማውን እንደሚሰቅል ይፋ ሆኗል።

ለ17 አመት በመርሲሳይዱ ክለብ ቆይታ ያደረገው ኮልማን፣ ከክለቡ ታሪካዊ ተጫዋቾች ተርታ ስሙን ማስፈር ችሏል።

ኤቨርተን ለረጅም አመት ግልጋሎት የሰጠውን ተጫዋች ጫማውን ከሰቀለ በኋላ በክለቡ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ እንዲቀላቀል ግብዣ አድርጎለታል።

አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስም፣ ኮልማን የአሰልጣኝ ቡድን አባላቶቻቸውን ቢቀላቀል ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሆኖም የ37 አመቱ ኮልማን ከውድድር አመቱ መጠናቀቅ በኋላ ስለሚኖረው ቆይታ አስተያየት አለመስጠቱ ተገልጿል።

አየርላንዳዊው ተከላካይ ኤቨርተንን የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 2009 ሲሆን፣ በ433 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ችሏል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbc

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.