አፍሪካ ሪ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩውን በአዲስ አበባ አከበረ!
#fastmereja : በአህጉሪቱ ቀዳሚው የኢንሹራንስ ተቋም የሆነዉ አፍሪካ ሪ (Africa Re) የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት ወርቃማ ኢዮቤልዩ እና 180ኛውን የቦርድ ስብሰባ አስመልክቶ በትላንትናዉ እለት በስካይላይት ሆቴል በተካሄደዉ የጋላ ኮክቴል አቀባበል በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።
በአህጉሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ስም ያለው ይህ ተቋም፣ ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረውን የስኬት ጉዞ በአፍሪካ የፖለቲካ መዲና አዲስ አበባ ማክበሩ የኢትዮጵያን የመድን ገበያ ያለውን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
እ.ኤ.አ. በ1976 በካሜሩን ያውንዴ የተመሰረተው አፍሪካ ሪ፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በድጋሚ መድን ዘርፍ ከቀዳሚዎቹ 40 ተቋማት ተርታ የተሰለፈ ግዙፍ ተቋም ነው፡፡
ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት የ42 አፍሪካ አገራት እና የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ከ110 በላይ አፍሪካውያን የመድን ኩባንያዎች፤እንዲሁም ከፈረንሳይ፣ ከጀርመን እና ከካናዳ የመጡ ዓለም አቀፍ አጋሮች ባለቤትነት ያለበት ተቋም ሲሆን በ2025 በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን 1.34 ቢሊዮን ዶላርየፕሪሚየም ገቢ ያስመዘገበ ሲሆን፣ 199 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱም ነዉ የተገለፀዉ።
የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሙስታፋ ኩሊባሊ (Mr. Moustapha Coulibaly) ለበዓሉ በሰጡት መግለጫ፣ “ይህ ወርቃማ ኢዮቤልዩ ለተቋሙ ብስለትን፣ ጥንካሬንና ጥበብን ይወክላል። አፍሪካ ሪ ከተቋምነት ባለፈ አፍሪካውያን በራሳቸው ሲተማመኑ ምን ዓይነት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ያሳየ የስኬት ታሪካችን ነው'' ብለዋል።
አቶ ሙስታፋ አክለውም ተቋሙ እ.ኤ.አ. በ2030 የገቢ መጠኑን ወደ 2.5 ቢሊዮን ዶላር፣ በ2035 ደግሞ 5 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ግዙፍ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሪ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ እንዳላት የተገለፀ ሲሆን ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በካሳንቺስ አካባቢ የገነባው ዘመናዊ ሕንፃ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ እንዲሁም ተቋሙ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንሹራንስ ዘርፍ ለማጠናከር በግብርና መድንና በቴክኒክ ዘርፎች ለአገር በቀል ኩባንያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ነዉ የተገለፀዉ።
በስካይላይት ሆቴል በተካሄደዉ የጋላ ኮክቴል ግብዣ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የአፍሪካ የፋይናንስ መሪዎችና ታዋቂ የንግድ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ይህም መድረክ አፍሪካ ሪ ወደፊት በአህጉሪቱና በኢትዮጵያ በሚኖረው የኢንቨስትመንት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት የሚደረግበት እንደሚሆን ተነግሯል።
አፍሪካ ሪ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በአህጉሪቱ ለሚከናወኑ የኢነርጂ፣ የግብርና፣ የቤት ልማትና የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የመድን ዋስትና ሽፋን (Cover) መስጠቱ ይታወሳል።

3 months ago