ኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ምክክር አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር በዋሽንግተን ዲሲ አካሂደዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራውና የጠቅላይ ሚኒስትር ኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ የብሄራዊ ደኀንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ያካተተ የልዑካን ቡድን ከአሜሪካ አቻዎቹ ጋር ተወያይቷል።
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ያካሄዱት የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ምክክር በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን፤ ይኸውም የኢኮኖሚ ብልጽግናን፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ የመከላከያ እና ጸጥታ እንዲሁም ቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ማስፈን የተመለከተ ነው።
የሁለትዮሽ መዋቅራዊ ምክክሩ የሀገራቱን ግንኙነት ዘላቂ በሆነ መንገድ የሚያስቀጥል እና የሚያጠናክር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

3 months ago