Logo
FastMereja
ገለልተኛ ሆነን ካየነው የሴዶ አካሄድ ትክክለኛ ሆኖ እናገኘዋለን።
ምክንያቱም የሚካሄደው ውድድር ላይ በቦታውም ሆነ በዩቲዩብ ወይም በቲቪ ብዙ ተመልካች የሚያዬው ሴዶን ለማየት ብሎ ነው።

ምክንያቱም ይሄንን ሰውየ እነ ጆኒንና እነ ንቃተ ህሊናን ሳናውቃቸው
በተለያዬ መንገድ እራሱን በደንብ ለህዝብ አስተዋውቋል።
ስለዚህ ህዝቤ ከጆኒ በላይ ለአመታት ሀሽ ሀሽ እያለ ጆሮውን ሲያግለው የኖረውን ሴዶን ይነርታል ወይስ ይነረታል የሚለው ነው የሚያጓጓው።

ይሄ ለሴዶ ገብቶታል ችግር የሆነው አንድ አቋም አልይዝ አለ አንዴ አስር ሚሊዮን አንዴ ሀምሳ ሚሊዮን የሚለውን አቋሙን ትቶ ከፋይት በፊት ይሄንን ያህል ክፈሉኝ ማለት ፕሮፌሽናልነት ነው።

አዘጋጆቹ ደግሞ አንድ ችግር አለባቸው። እሱን የፈራ አስመስለው የሚያዋክቡበት መንገድ ልክ አይደለም። ካሸነፍክ አስር ሚሊየን ውሰድም አይባልም።

ከፋይት በፊት አምስት ሚሊዮን ነው የጠየቀው አደል በዛ ጉዳይ ተደራድረው ከፋይት በፊት አምስት መቶ ሺ ወይ ሌላም ከፋይት በኋላ ደግሞ ለአሸናፊ ይሄንን ያህል ለተሸናፊ ይሄንን ያህል ተብሎ ነው መግለጫ የሚሰጠው! ውርርድ አስመሰለባቸው ካሸነፍክ አስር ካላሸነፍክ በቁምጣህ አሉት😂

ለወደፊቱም እንደዚህ አይባልም በርግጥ እረዳችኋለሁ ዛሬ ለሴዶ ቅድሚያ ክፍያ ከሰጣችሁ ነገ ሁሉም ተወዳዳሪ ብር ሊጠይቃችሁ እንደሚችል ፈርታችሁ ነው።

ስለዚህ በስርዓት ተደራደሩና ተስማሙና ቅድሚያ ክፍያውን አቅርቡለት። ያኔ ብሩን ተሰጥቶት ወደ ኋላ ካለ በጋራ ፈሪ እንለዋለን!

አሁን ላይ ግን ሴዶን ፈሪ የምትሉበት የማዋከብ ሙድ ልክ አይደለም! Via Koan AD

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.