Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በህይወት እንዳሉ እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ መሪው በመጋቢት ወር መጀመሪያ አካባቢ የተገደሉትን አባታቸውን ለመተካት ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ በአደባባይ ታይተውም ሆነ ድምፃቸው ተሰምቶ አያውቅም።

ኔታንያሁ ከሲቢኤስ የቴሌቪዥን ጣቢያ "60 ሚኒትስ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ስለ አዲሱ መሪ (ታናሹ ኻሜኒ) አካላዊ ሁኔታ እና የአመራር ተጽዕኖ ተጠይቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱም፤ "በህይወት እንዳሉ አስባለሁ። ነገር ግን በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለመናገር ይከብዳል። የሆነ የመሬት ውስጥ መሸሸጊያ (bunker) ወይም ሚስጥራዊ ቦታ ውስጥ ተደብቀዋል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ሞጅታባ "ስልጣኑን እና ተጽዕኖውን ለማሳረፍ እየሞከረ ነው" ካሉ በኋላ፣ ነገር ግን ይህ የሞጅታባ ስልጣን ከቀድሞው መሪ (ከአባታቸው አሊ ኻሜኒ) ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ያነሰ መሆኑን ገምግመዋል።

25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.