ኢራን በዓለም ዋንጫ ላይ ለሚኖራት ተሳትፎ ዋስትና ጠየቀች
ኢራን በዓለም ዋንጫ ላይ እንደምትሳፍ ገልጻ ነገር ግን ከፊፋ እና ጨዋታውን ከሚያስተናግዱ አገራት ዋስትና እንደምትፈልግ አስታወቀች።
የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዓለም ዋንጫ ላይ “ከምናምንብት፣ ከባሕላችን እና ከቁርጠንነታችን ሳናፈገፍግ” እንሳተፋለን ሲሉ አረጋግጠው፣ አዘጋጅ አገራት “ስጋታችንን ከግምት ውስጥ እንዲያስገቡልን እንፈልጋለን” ብለዋል።
የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ መሟላት አለባቸው ያላቸውን ነገሮች ያቀረበው ፕሬዚዳንቱ መሃዲ ታጅ ባለፈው ወር ካናዳ በተካሄደው የፊፋ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ሲጠይቁ ቪዛ በመከልከላቸው ነው።
ታጅ አገራቸው በዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ መሟላት አለባቸው ያሏቸውን ባለ አስር ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን ለፊፋ ማቅረቧን ተናግረዋል።
የዓለም ዋንጫ በሜክሲኮ በካናዳ እና በዩናይትድ ስቴትስ አዘጋጅነት ከሰኔ 4 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ይካሄዳል።
ቅዳሜ ዕለት በመግለጫው ላይ ከሰፈሩት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ሁሉም በእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወታደራዊ ስልጠና ያጠናቀቁትን ጨምሮ ከቡድኑ ጋር የሚጓዙ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች እና ባለሥልጣናት ቪዛ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ነው።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ በካናዳ እና አሜሪካ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀ ሲሆን፣ መሃዲ ታጂ ወደ ካናዳ መግቢያ ቪዛ የተከለከሉት ከወታደራዊው ተቋሙ ጋር ባላቸው ግንኙነት ነው ተብሏል።
ኢራን ለእግር ኳስ ቡድኗ፣ ለባንዲራዋ እንዲሁም ለብሔራዊ መዝሙሯ ተገቢው ክብር አንዲሰጥ እንዲሁም በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች እና ስታዲየሞች ጥበቃ እንዲጠናከርላት ጠይቃለች።
የተወሰኑት የኢራን ጥያቄዎች ፊፋ በቀላሉ እንዲሟሉ ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ናቸው።
ነገር ግን ከቪዛ፣ የድንበር ቁጥጥር እና ደህንነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ከፊፋ ይልቅ የአገራቱ ሕግ ስር የሚወድቁ ናቸው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የኢራን የእግር ኳስ ቡድን መትቶ በዓለም ዋንጫ ላይ ቢካፈል ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ነበር።
ነገር ግን ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያላቸው አባላት ክልከላ እንደሚገጥማቸው አስጠንቅቀዋል።
BBC

27 days ago