17ኛው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተካሄደ
#ethiopia | ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 17ኛው የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በዚህ ስፖርታዊ ኩነት ላይ ከ2,000 በላይ ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶችም ቀርበዋል።
ዕድሜያቸው እስከ 14 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች የተሳተፉበት ይህ ውድድር በለጋ ዕድሜያቸው ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን እንዲላመዱና ማህበራዊ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ተሳታፊዎቹ እንደ ዕድሜያቸው በምድብ ተከፋፍለው የሜዳ ላይ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን ይህም ከ5 እስከ 14 ዓመት ያሉ ህፃናትን ያካተተ ነበር።
የዘንድሮው የሩጫ መርሃ ግብር ከአለም አቀፍ የእናቶች ቀን ጋር መገጣጠሙ ለዝግጅቱ ልዩ ድምቀት የሰጠው ሲሆን ህፃናቱም ለእናቶቻቸው ያላቸውን ፍቅር በልዩ ልዩ ስነ ስርዓቶች ገልጸዋል።
የአውሮፓ ቀን የህፃናት ሩጫ በየዓመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ስፖርታዊና ባህላዊ ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በመጨረሻም በውድድሩ ለተሳተፉ ህፃናት ሁሉ የእውቅና ሜዳሊያ የተሰጠ ሲሆን አሸናፊ ለሆኑት ደግሞ ልዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።
ዝግጅቱ በሙዚቃና በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ታጅቦ በታላቅ ደስታ ተጠናቅቋል።
#europeday #greatethiopianrun #childrenrun #sport #mothersday #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

25 days ago