የቃላት ጦር ወይስ የሰላም ድልድይ?
*************
(የዕለቱ መልዕክት)
የኢትዮጵያ ሚዲያ ዛሬ የቆመበት አውድ ከታሪካዊ ስንክሳሮች ተላቆ፣ ለነገዋ ሀገር ግንባታ የሚሆን አዲስ ምዕራፍ እንዲከፍት የሚጠይቅ ወሳኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ ይገኛል። የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዞ የሚዲያን እምርታና የትርክት ግንባታ ጥበብን እንደ ዋና መሪ ኮምፓስ መጠቀም እንደሚገባ ያመላክታል።
ኢትዮጵያ የተሰራችበት አፈር አንድነት ላይ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን በምንጋራው አፈርና ጭቃ ላይ መሰረታዊ ልዩነት የለንም። ሆኖም ችግሩ የሚጀምረው ይህ ጭቃ ተቦክቶ ቅርፅ መያዝ ሲጀምር ነው። ልዩነታችን የተፈጠረው ቅርፅ ከወጣለት በኋላ "ጀበናው ይርዘም ወይስ ሲኒው ይስፋ" በሚሉ የቅርፅ ሽኩቻዎች ላይ ነው። ይህም “የቆየውን አፈር አዲስ ሸክላ ሰሪ አይንቀውም” እንደሚባለው ነው፤ መሰረታችን አንድ መሆኑን ዘንግተን በውጫዊ ቅርፅ ላይ እንጣላለን።
የሚዲያ ተቋማት ለዘመናት ትኩረት ሲያደርጉ የቆዩት በዚህ የቅርፅ ልዩነት ላይ እንጂ ሁሉም እኩል በሚጋራውና መሰረት በሆነው የጋራ ማንነት አፈር ላይ አይደለም።
ህዝብ ለዘመናት በደምና በአጥንት የተሳሰረበትን ታሪክ በመበጠስ፣ ለአንድ ወቅት ግጭቶች ቅድሚያ መስጠት የሚዲያ ሰብዕናን የሚያጎድል የ"አርዕስተ ዜና ንግድ" ነው። ሚዲያው ቁምነገር ከማውጣት ይልቅ ጩኸት ላይ ብቻ መተኮር የለበትም። ጥልቀት የሌላቸውና ህዝብን የሚያጋጩ አርዕስቶችን መሸጥ ሀገርን ለከፋ አደጋ አሳልፎ መስጠት ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) እንዳሉት እውነተኛ ጋዜጠኝነት ከግል ጥቅሙ ገለልተኛ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከሀገሩ ህልውና ገለልተኛ መሆን አይችልም። ሚዲያው ጥላቻ በተዘራባት ምድር ላይ ዳግም የጥፋት ዘርን ማሰራጨት ሳይሆን "እንዴት እናቅናው?" በሚል የፈውስ ጥበብ ላይ ማተኮር አለበት። “በቁስል ላይ እንጨት” እንደሚባለው ስንጥቆችን ከማስፋት ይልቅ የሰላም ድልድይ መሆን ይገባዋል። የቃላት ጦር ከመድፍ ባልተናነሰ ሀገርን የማፈራረስ አቅም አለውና።
ነፃነትን ማግኘት ስኬት ቢሆንም በኃላፊነት ማስተዳደር ግን የብስለት ምልክት ነው። “ካፈሰሱት አይታፈስ፣ ካመለጡት አይመለስ” እንደሚባለው፣ በሚዲያ የሚወረወር ቃል አንዴ ከወጣ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን ይችላል። ነፃነትን ለሀገር ማፍረሻነት መጠቀም ነፃነትን ማርከስ ነው። በሚዲያ ስራ ውስጥ ህግና ሙያዊ ስነ-ምግባርን ማስጠበቅ የጥንካሬ መገለጫ እንጂ የነፃነት እጦት አይደለም።
በቴክኖሎጂው ዘመን መረጃ (Data) አዲሱ የዓለም ኃይል ነው። ሚዲያዎች ስለ ፖለቲካ ትኩሳት ብቻ ሳይሆን ስለ ንግድና ምርታማነት የሚያስተምሩ የዕውቀት ምንጮች መሆን አለባቸው። የኢትዮጵያ ሚዲያ አንዱ ስንክሳር ጉዳይን መሸጥ ሳይሆን አርዕስተ ዜናን መሸጥ ላይ ማተኮሩ ነው። “የሸመቱት እንጂ የፈተሉት አይለብስም” እንዲሉ፣ የራሳችንን መረጃና ዳታ ጠብቀን ካልያዝን የሌላው ትርክት ሰለባ መሆናችን አይቀርም።
በመጨረሻም፣ ሚዛናዊነት የረጅም ጊዜ ድል ቁልፍ ነው። ዋልታ ረገጥነትና ጽንፈኝነት መጨረሻቸው መሰበር መሆኑን ታሪካችን አስተምሮናል። “ካልከረረ አይበጠስም” እንደሚባለው፣ ሁሉንም ነገር አክሮ መስራት ለውድቀት ይዳርጋል። ስለዚህ ሚዲያው ከሸቀጥነት ወጥቶ ለሀገር ግንባታ የሚተጋ የሰላም ድልድይ መሆን አለበት።
እውነትን መናገር ዋጋ ቢያስከፍልም፣ “እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራል” እንደሚባለው መጨረሻው ድል ነው። ኢትዮጵያን የጋራ ቅርፅ የምናስይዛት የጋራ ማንነታችንን በሚያጸኑና በውይይት በሚያምኑ ሚዲያዎች አማካኝነት ብቻ ነው። የሚዲያ ሰዎች በቃላት ጦር ምትክ የሰላም ድልድይ በመሆን፣ ጥላቻን በፍቅር፣ ድንቁርናን በዕውቀት የሚተኩ የብርሃን ወታደሮች መሆን ይጠበቅባቸዋል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

3 months ago