Logo
SeledaPost
የአምስት ዓመት ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው የ65 ዓመት ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በሰገን ዙርያ ወረዳ ውስጥ የስልሳ አምስት አመቱ ግለሰብ በአምስት ዓመትታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ መሆኑን የወረዳው ፍርድቤት ገልፀዋል።የሰገን  ዙርያ ወረዳ ፍርድ ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ተስፋዬ እንደገለጹት ተከሳሹ አቶ ሲዳሞ ገልገሎ የተባለ የስልሳ አምስት አመት ግለሰብ የአምስት አመት ልጅ ማንም በሌለበት የአስገድዶ መድፈር  ወንጀል እንደፈጸሙባት ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ፖሊስም የአምስት ዓመቷን ታዳጊ በህክምና ምርመራ በማስደገፍ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለአቃቢ ህግ ልኳል።የሰገን ዙሪያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ዓቃቤ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ የሚያስረዱ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ተከሳሹ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛነቱን አረጋግጧል።በዚሁ መሰረት ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሲዳሞ ገልገሎ በፈፀመው የከፋ ወንጀል ተጸጽቶ እንዲታረም እና ሌሎች መሰል እኩይ ተግባር እንዳይፈጽም ትምህርት እንዲሆን በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ ተቋሙ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ህብረተሰቡ ህፃናትን ከእንዲህ ዓይነት ጥቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.