Logo
Getu Temesgen
ኖቲንግሀም ፎረስት በቼልሲ ላይ ድል በመቀዳጀት በሊጉ የመቆየት ተስፋውን አጠናከረ
#ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኖቲንግሀም ፎረስት ቼልሲን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በስታምፎርድ ብሪጅ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ታይዎ አዎኒ ሁለት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ ቀሪዋን አንድ ግብ ደግሞ ኢጎር ጄሱስ አስቆጥሯል።

ለቼልሲ ብቸኛዋን ግብ ጃኦ ፔድሮ ማስቆጠር ቢችልም ቡድኑን ከሽንፈት ሊታደገው አልቻለም።

ቼልሲ በሊጉ ብቻ በተከታታይ ስድስት ጨዋታዎችን ለመሸነፍ የተገደደ ሲሆን ኖቲንግሀም ፎረስት በበኩሉ ነጥቡን ወደ 42 በማሳደግ በደረጃ ሰንጠረዡ 16ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
#football #epl #nottinghamforest #chelsea #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.