በአሜሪካ ተይዘው ከነበሩት የኢራን መርከብ ሠራተኞች መካከል ስድስቱ ተለቀቁ
*****************
በቅርቡ በአሜሪካ ባሕር ኃይል ተይዛ ከነበረችውና ‘ቱስካ’ (Touska) ከተሰኘችው የኢራን የጭነት መርከብ ላይ ስድስት ሰራተኞች ተለቀው ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።
አሁንም በአሜሪካ ቁጥጥር ሥር የሚገኙት ቀሪዎቹ 22 ሰራተኞች እንዲለቀቁ የኢራን ባለስልጣናት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የዜና ምንጩ አክሎ ገልጿል።
አሜሪካ መርከቧን የያዘችው እ.አ.አ በኤፕሪል 20 ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ መርከቧ "የሆርሙዝ የባሕር መስመርን ለቃ እንድትወጣ የተሰጣትን ትዕዛዝ ባለማክበሯ ነው" ተብሏል።
ኢራን የሆርሙዝ የባሕር መስመርን መዝጋቷን ተከትሎ፣ አሜሪካም ከአፕሪል 13 ጀምሮ በኢራን ላይ የባሕር እገዳ ጥላ ትገኛለች።
#middleeast #us #iran #hormuz #touska #ebc

1 month ago