የነዳጅ ዋጋ ንረቱ ጫና በቀጥታ ኅብረተሰቡ ላይ እንዳያርፍ መንግሥት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ ነው - አቶ አሕመድ ሽዴ
*************
በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የሚፈጠረውን የኑሮ ውድነት ለመከላከል እና በተለይም የዋጋ ንረቱ ወደ ኅብረተሰቡ እንዳይተላለፍ ለማድረግ መንግሥት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስተሩ አሕመድ ሽዴ ገለጹ።
መንግሥት በየወሩ የ20 ቢሊዮን ብር ድጎማ እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት የገንዘብ ሚኒስትሩ፣ እስከአሁን ለነዳጅ የተደረገው አጠቃላይ ድጎማ ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ገልጸዋል።
አሁን የናፍጣ አቅርቦት መጠን ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት መደበኛ ሁኔታ መመለሱን አንስተው፣ ይሁን እንጂ መንግሥት የዋጋ ጭማሪው ጫና በቀጥታ በሕዝቡ ላይ እንዳያርፍ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ድጎማውን አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
መንግሥት ይህን ከፍተኛ የድጎማ ወጪ የመደበው ሀገራዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ይበልጥ ለማቀላጠፍ እና የታለመውን የ10.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማሳካት በማሰብ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ኅብረተሰቡ ይህን በከፍተኛ ወጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚቀርበውን ነዳጅ ከብክነት በጸዳ መልኩ በመጠቀም ለታለመለት የኢኮኖሚ ዓላማ ብቻ እንዲውል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።
በመንግሥት በኩልም የነዳጅ አቅርቦቱን እና ሥርጭቱን አፈጻጸም በቅርበት ለመከታተል የሚያስችል ግብረ ኃይል ተቋቁሞ አስፈላጊውን የቁጥጥር ሥራ 24 ሰዓት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #economy #resilience #fuel #subsidy

3 months ago