Logo
Getu Temesgen
አርሰናል : ኡጋንዳዊ ደጋፊ ክስ መሰረተ
#ethiopia | ​አርሰናል በሜዳው በቦርንማውዝ መሸነፉ ያስቆጣው ኤሪክ ኪያማ የተባለ ኡጋንዳዊ ደጋፊ፣ በክለቡ፣ በተጫዋቾቹ እና በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ላይ የክስ ማስጠንቀቂያ ላከ።

​ የክሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​የሙያ ግዴታን መዘንጋት
ተጫዋቾቹ ምንም ዓይነት የማሸነፍ ፍላጎትና ጥረት ሳያሳዩ በመጫወታቸው "Professional Negligence" ፈጽመዋል ብሏል።

​የአርቴታ የታክቲክ ብቃት ማነስ
አሰልጣኙ ጨዋታውን መምራት ባለመቻሉና ለተፈጠረው ለውጥ ፈጣን ምላሽ ባለመስጠቱ ክስ ቀርቦበታል።

​የስነ-ልቦና እና የገንዘብ ኪሳራ
ደጋፊዎች ጊዜያቸውንና ስሜታቸውን ለክለቡ ቢሰጡም፣ ክለቡ ግን ግዴለሽነት በማሳየቱ "actionable distress" (ክስ የሚያስመሰርት ጭንቀት) ፈጥሮብኛል ብሏል።

​የብራንድ ማጭበርበር፦
"Victory Through Harmony" የሚለው የአርሰናል መርህ በሜዳ ላይ ከታየው ሽንፈት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ደጋፊዎችን ማጭበርበር ነው ሲል ገልጾታል።

​ኤሪክ አክሎም ክለቡ አፋጣኝ ማብራሪያና የታረመ አፈጻጸም ካላሳየ የካሳ ክፍያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል።

​#getu #arsenal #mikelarteta #lawsuit #erickyama #uganda #gooners #afcbournemouth #premierleague #footballnews #አርሰናል #ሚኬልአርቴታ #ክስ #ኡጋንዳ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.