Logo
FastMereja
ቴዲ አፍሮ ስለ አልበሙ

​#fastmereja I ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) "ኢቶሪካ" የተሰኘውን አዲስ የሙዚቃ አልበሙን የፊታችን ሐሙስ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

​ለረጅም ጊዜ በአድናቂዎቹ ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የቆየው ይህ አልበም፣ በዕለቱ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በድምጻዊው ይፋዊ የዩቲዩብ ገጽ (Teddy Afro Official) ላይ ተደራሽ እንደሚሆን ተገልጿል። ድምጻዊው ይህንኑ የምስራች "የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም" በሚል መሪ ቃል በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት አረጋግጧል።

​ይህ አዲስ አልበም ከዓመታት ቆይታ በኋላ የሚመጣ በመሆኑ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

​ሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም.

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.