Logo
Getu Temesgen
ጅቡቲ የደረሱት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች
#ethiopia ||ወደ ጅቡቲ ወደብ የደረሱ ሶስት ግዙፍ መርከቦች በኢትዮጵያ አጋጥሞ ለነበረው የነዳጅ እጥረት መጠነኛ እፎይታ እንደሚያመጡ ተገለጸ።

ከመጋቢት 19 እስከ 23 ባሉት ቀናት የደረሱት እነዚህ መርከቦች በአጠቃላይ 143 ሺህ ሜትሪክ ቶን የጄት ነዳጅ እና ናፍጣ ይዘው መምጣታቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ስላንዣበበው ስጋት አስጠንቅቋል።

በባህረ ሰላጤው አካባቢ እየታየ ያለው ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችን በማስተጓጎል እና የጭነት ትራንስፖርት ዋጋን በማስወደድ በቀጣናው ሀገራት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሊያስከትል እንደሚችል የድርጅቱ ትንታኔ አመልክቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #capitalnews #ethiopia #djibouti #fuelshortage #imf #eastafrica #globaleconomy #geopolitics #newsupdate #ነዳጅ #ኢትዮጵያ #ጅቡቲ #ኢኮኖሚ

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.