Logo
Getu Temesgen
የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በእስዋቲኒ መኮብለላቸው ተሰማ
#ethiopia | የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ባህር ግመሎች) ለዓመታት ከአህጉራዊ ውድድሮች ርቆ ከቆየ በኋላ፣ በቅርቡ ባደረገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ውጤታማ ሆኖ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል መቀላቀሉ የሚታወስ ነው። ሆኖም ይህን ደስታ የሚያደበዝዝ ዜና ከስፍራው እየወጣ ይገኛል።
ከቡድኑ ስብስብ ጋር ወደ እስዋቲኒ ተጉዘው ከነበሩት የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች መካከል ሰባቱ (7) መጥፋታቸው ተረጋግጧል።

ቡድኑ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ባከናወነባት እስዋቲኒ።በስብስቡ ውስጥ ተካተው ከነበሩ 10 የሀገር ውስጥ ተጫዋቾች መካከል 3ቱ ብቻ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ፣ 7ቱ ግን እዛው ቀርተዋል።

ተጫዋቾቹ ብሔራዊ ቡድኑ ረጅም ጊዜ ከቆየበት እገዳ ተላቆ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ እንዲመለስ ትልቅ ግዳጅ ከተወጡ በኋላ ነው የመመለስ ፍቃደኛ ያልሆኑት።

የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት በሚደረጉ ውድድሮች ላይ መሰል ድርጊቶችን ሲፈጽሙ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የአሁኑ አጋጣሚ ቡድኑ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ በተመለሰበት ማግስት መከሰቱ ትኩረት ስቧል ያለው ቲክቫህ ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #eritrea #redseacamels #afcon2025 #footballnews #eswatini #africacupof Nations #breakingnews #eritreanfootball

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.