Logo
Getu Temesgen
ቼልሲ ፖርት ቫልን 7 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜ ገባ
#ethiopia | ​በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት የሊግ አንዱን ፖርት ቫልን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። በዚህም ከማንችስተር ሲቲ በመቀጠል ለግማሽ ፍጻሜው የደረሰ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።

በወጣቱ አሰልጣኝ ሊያም ሮሰኒየር የሚመራው ቼልሲ በየተራ ግቦችን አከታትሏል፦

​ጆርል ሃቶ
​ጃኦ ፔድሮ
​ቶሲን አዳራቢዮ
​አንድሬ ሳንቶስ
​ኤስቲቫኦ ዊሊያን
​አሌሃንድሮ ጋርናቾ
​ጋብርኤል (በራሱ መረብ ላይ)

​በሊግ አንድ የሚሳተፈው ፖርት ቫል ጠንካራ ተቃውሞ ለማሳየት ቢሞክርም፣ በቼልሲ የፊት መስመር ተጫዋቾች ብቃት ተሸንፎ ጉዞው በሩብ ፍጻሜው ሊገታ ችሏል።

አሁን የሁላችንም ዓይን ወደ ምሽቱ 4:00 ጨዋታ ዞሯል፦

🔴 አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን (መድፈኞቹ ሶስተኛው የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን ወደ ሜዳ ይገባሉ)።

​#getu #facup #chelseafc #portvale #stamfordbridge #goalfest #londonisblue #footballethiopia #mancity #arsenal #ቼልሲ #ኤፍኤካፕ #እግርኳስ #ድል #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.