ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሚያዝያ ወር ሊቀመንበርነትን ተረከበች
#ethiopia | ኢትዮጵያ በያዝነው የሚያዝያ ወር የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤትን በሊቀመንበርነት ለመምራት ኃላፊነቷን መረከቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። አገሪቱ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ምክር ቤቱን በድጋሚ ከተቀላቀለች በኋላ በሊቀመንበርነት ስትሰየም ይህ የመጀመሪያዋ ነው።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መሠረት፤ ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የሥራ ቆይታዋ የምክር ቤቱን ቁልፍ አጀንዳዎች በይፋ መምራት ትጀምራለች። በተለይም በአኅጉራዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች፣ ሀገር በቀል መፍትሔዎች እና ጭብጥ ተኮር በሆኑ አበይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን በግንባር ቀደምትነት የምትመራ ይሆናል።
የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ2004 ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያ የመሥራችነት ሚና የነበራት ሲሆን፣ እስካሁንም አራት ጊዜ በምክር ቤቱ ውስጥ በአባልነት አገልግላለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ብስራትfm #ኢትዮጵያ #አፍሪካ_ሕብረት #ሰላምና_ፀጥታ #ውጭ_ጉዳይ #ethiopia #africanunion #au_psc #peaceandsecurity #diplomacy #africanews

6 months ago