ያለደረሰኝ ሽያጭ የፈፀሙ 55 ግብር ከፋዮች በጽኑ እስራት ተቀጡ
#fastmereja I አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውኑ የተገኙ 55 ግብር ከፋዮች ከ1 ዓመት እስከ 2 ዓመት ከ6 ወራት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ ቅጣት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ባለፉት ስምንት ወራት ባካሄደው ተከታታይ የኦፕሬሽን ስራ 294 ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ገልጿል።
የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለማስፈን ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ባከናወነው እርምጃ፣ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
እንደ ቢሮው መረጃ ክሳቸው በፍርድ ቤት ከታዩ 55 ግብር ከፋዮች መካከል ከፍተኛው ቅጣት 2 ዓመት ከ6 ወራት እስራት ሆኖ ተመዝግቧል።
በአጠቃላይ 294 ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 239 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በፖሊስና በአቃቤ ህግ እየታየ ይገኛል።
ኦፕሬሽኑ በጎማና መኪና መለዋወጫ፣ በኤሌክትሮኒክስ፣ በኮንስትራክሽን ግብአቶች፣ በስጋ ቤቶች፣ በሱፍ ልብስና በወለል ምንጣፍ ንግድ ላይ ያተኮረ ነበር።
ቢሮው የመንግስትን ጥቅም ለማሳጣትና የታክስ አስተዳደር አዋጅን በመጣስ ያለደረሰኝ ሽያጭ የሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቧል። የንግዱ ማህበረሰብ ግብይቱን በደረሰኝ ብቻ እንዲያከናውን፣ ህብረተሰቡም መሰል ጥሰቶችን ሲመለከት በ7075 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

2 months ago