የቡና ምርት ወጭ ንግድን ለማሳለጥ በደረቅ ወደቦች ያሉ ኮንቴነሮች በፍጥነት እንዲወጡ ተጠየቀ
በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት የባህር ትራንስፖርት እንቅስቃሴ በመገደቡ፣ በኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ላይ የባዶ ኮንቴነር እጥረት ማጋጠሙ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ እንዳለዉ፤ በተለይም ወቅቱ ከፍተኛ መጠን ያለው የቡና ምርት ለዓለም ገበያ የሚቀርብበት ወቅት በመሆኑ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በአሁኑ ወቅት በሞጆ እና ቃሊቲ ደረቅ ወደቦች የገቢ ጭነት የያዙ 2,005 ባለ 20 ጫማ እና 2,471 ባለ 40 ጫማ፣ በድምሩ ከ4,400 በላይ ኮንቴነሮች ይገኛሉ።
አስመጭዎች እነዚህን ኮንቴነሮች በፍጥነት አውጥተው ተመላሽ እንዲያደርጉ ክትትል እንዲደረግና ኮንቴነሮቹ ለወጭ ንግድ (ኤክስፖርት) እንዲውሉ አስፈላጊው ርብርብ እንዲደረግ ለግምሩክ ኮሚሽን ባለስልጣኑ ጥሪ ማቅረቡን ቅዳሜ ገበያ የደረሳት መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም በዩኒሞዳል ሥርዓት ወደ ሀገር የገቡ ኮንቴነሮች ያለ መርከብ ወኪሎች ማረጋገጫ በባዶ ወደ ጅቡቲ እንዳይመለሱ የተሰጠው አቅጣጫ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ለቡና እና ለሌሎች የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች ወጭ ንግድ ቅድሚያ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
seledadotio

4 months ago