የደም ግፊት(HTN)
ሰውነተችን የራሱ የሆነ የደም ቅዳ ቱቦ ግፊት(arterial pressure) አለው።በአማካይ 90-120/60-80 mmHg እንደሆነ በሳይንስ ይታመናል። ከዚህ አማካይ ከፍ ብሎ ሲገኝ የደም ግፊት(HTN) ተብሎ ይጠራል።
በተለምዶ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የደም ግፊት ተብሎ የሚከፈል ሲሆን ለህክምና በሚያመች መልኩ በ4 ደረጃ ተከፋፍሎ ይገኛል።
መንስኤ
ከመንስኤ አንፃር ፕራይሜሪ( esential HTN) እና secondary HTN በመባል ይታወቃሉ።
የመጀመሪያው አይነት ምክንያት አልባ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የታወቀ መንስኤ ያላቸው የኩላሊት ችግር ፣የሆርሞኖች መዛባት የመሳሰሉ መንስኤዎች ይኖሩታል።
በአብዛኛው (ሰማኒያ በመቶ) የመጀመሪያው አይነት የደም ግፊት ሲይዝ ሃያ በመቶ ደግሞ ሁለተኛው አይነት የደም ግፊት ድርሻውን ይወስዳል።
ምልክቶች
በአብዛኛው የደም ግፊት ምንም ምልክት የማያሳይ ሲሆን ራስ ምታት ፣ የአይን ብዥታ ፣ ራስ መሳት የመሳሰሉ ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል።
ምልክት ከማያሳዩ( silent killer) ተብለው ከሚጠሩ ህመሞች አንዱ ስለሆነ የደም ግፊት በየጊዜው መለካት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
አጋላጭ ባህሪያት
• ያለ ቅጥ ውፍረት(obesity)
• ሲጋራ ማጨስ
• ጭንቀት
• አልኮል መጠቀም
• ጨው አብዝቶ መጠቀም
• የቤተሰብ የደም ግፊት መኖር
• የእንቅስቃሴ ማነስ
• እና ሌሎችም
ህክምናው
ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶች ሳያቋርጡ እና መጠኑን ሳያዛቡ መውሰድ እና ከታች የተዘረዘሩ መከላከያ መንገዶችን መጠቀም።
ተያያዥ ችግሮች
የደም ግፊት ህመም ከሚከተሉት ህመሞች ጋር በተዛማጅነት ሊከሰት ይችላል።
• ከስኳር
• ከውፍረት
• ከኮሌስትሮል።
መከላከያ መንገዶች"
የህይወት ሚዛን ለውጥ(life style modifications) ህይወት ሁሌም ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ይፈልጋል።
በየቀኑ የምንመገባቸው ምግቦች የሚሰጡን ሃይልና የምናቃጥለው ሃይል መመጣጠን ይኖርበታል።
ካልሆነ ግን በረጅም ጊዜ የሚፈጠሩ የጤና እክሎች እንጋለጣለን ከእነዚህም መካከል የደም ግፊት፣ ስኳር ፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል ዋናዋናዎቹ ናቸው።
አመጋገብ ማስተካከል አራቱ ነጫጭ የምግብ ሴጣናች ማለትም ስኳር፣ጨው ፣ጮማ እና አልኮል ሲወሰዱ ጣፋጭ ሆነው የረጅም ጊዜ መዘዛቸው ግን የከፋ ነው።
በተቻለ መጠን የደም ግፊት ታካሚ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ጤነኛ ሰው እነዚህን መቀነስና አትክልት ፍራፍሬ መመገብ ያስፈልጋል።
seledadotio

4 months ago