Logo
Getu Temesgen
8ኛው ዙር ብስክሌት በአዲስ ወርኃዊ ፌስቲቫል! ! "ብስክሌት በአዲስ" በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ
#ethiopia | ነፍ ኮምዩኒኬሽን እና ኤቨንት ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ ያዘጋጁት ስምንተኛው ዙር “ብስክሌት በአዲስ” ወርኃዊ ፌስቲቫል በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

ፌስቲቫሉ ከሲ ኤም ሲ አደባባይ እስከ ፍየል ቤት ድረስ በተዘጋጀ መርሐግብር በብዙ ተሳታፊዎች የተካሄደ ሲሆን የብስክሌት ወዳጆች፣ ወጣቶች ህፃናት እና ቤተሰቦች በብዛት ተሳትፈዋል።

በዛሬው ፌስቲቫል የባህል ቡድኖች መዚቃቸውን ለተሳታፊው ሲያቅርቡ ምግብና መጠጦች እና የህፃናት መዝናኛዎች ቀርበውበታል።

በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊዎች በታላቅ ደስታ ብስክሌት በመንዳት ያሳለፉ ሲሆን ይህ ዝግጅት በቀጣይ ወር ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተሳታፊ እንዲሆን ተጋብዟል።
#neff Communication & Event

''ብስክሌት በአዲስ” ፌስቲቫል በወር አንድ ጊዜ የሚካሄድ ኩነት ሲሆን አዲስአበባ ከተማ በመጀመር በተለያዩ የክልል ከተሞች በቅርብ ጉዞ ይጀመራል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.