Logo
Getu Temesgen
ከጉንችሪየ ለኢትዮጵያ የተበረከተው አዲስ አዳጊ ኮከብ
#ethiopia | እኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ደጅ ከረገጥኩበት እለት ጀምሮ ፣ እያስደመመኝ ነው።አስቀድሞ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ከደረሰ በኋላ ለኪነ ጥበብ ያለው ልዩ መሰጠትና ጉጉት ስላየሁ፣ ወደ ቢሮዬ ጠርቼው አናግሬው ነበር። የሰጠነው የተማሪዎች ካውንስል የህዝብ ግንኙነት ነበር።

ግቢው ራሱን ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ብዙ ነገሮች እንዳሉት በዚህም በዞኑ ውስጥ ያለውን አቅም በደንብ ለመጠቀም እንደሚረዳው፣ ዞኑም ይሁን ዩኒቨርሲቲው ከእርሱ የሚፈልጉት ብዙ ነገር እንዳለ ነግሬው ተስማምተን ተለያየን።

ቆይቶ ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለውድድር ማስታወቂያ ሲወጣ ስላላስቻለው መጥቶ ተወዳደረ። ተሳክቶለትም አለፈ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲአትር ት/ቤት ተቀላቀለ። በድጋሚ ወልቂጤ እንዲቀር ባሳምነውም በአገር ደረጃ ከፍ ያለ ነገር ሰርቼ ህዝባችንን ማስጠራት ይሻላል ነበር ያለኝ።

መልካም እድል ተመኝቼለት ተሰናበትን። አይደርስ የለ ፍረሽ ሆኜ ስድስት ኪሎ ስገባ እነ ፍርፍር ተራን ያስፎሸኝ እሱ ነው። ናኦድ አሁን የዩኒቨርሲቲዝ ከባድ የቲአትር ሰው የመድረክ መሪ እና አጋፋሪ ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደሞ ትልቁን የአገር ዋርካ በመድረክ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ድጌ ኮራሁበት። እናንተም ማንኛውም አይነት የጉራጊኛና የአማርኛ የመድረክ ስራ ሲኖራችሁ ደውላችሁ አሰሩት።በእርግጥም ትወዱታላችሁ። ተራእንረ ኧሰሞ!

ስልኩ: +251994691902

© Remedan Nürgeta

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.