ማነው የእመቤታችን ወዳጅ? ኑ በገዳም ለምትገኘው የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን የ21,000 ብር ቻሌንጅ እንጀምር!
ጎንደር ጎርጎራን ስናስብ ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የጣና ሞገስ የሆነውን የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳምን በዓይናችን ላይ አለመሳል ከባድ ነው::
ይህ ገዳም በውስጡ የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያለው ሲሆን ከግዝት ቅጥር ውጭ እህቶችና እናቶች እንዲቆርቡ የሚያስችል በቂ ስፍራ በቤተክርስቲያን ስለሌለ ሥርዓቱ የሚፈጸመው በድንኳንና በዳስ ነው:: በተለይም መስከረም 14 እና መጋቢት 27 ለበዓለ ንግሥ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ ከተለያየ ሥፍራ ስለሚመጣ ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ ይፈጠራል:: አባቶች ክቡር ስጋውንና ቅዱስ ደሙን በውጭ ያቀብላሉ:: ይህ ደግሞ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን ከመቆርቆር አንጻር ሲታይ ደግሞ ልብ ዝቅ ያደርጋል:: ይህንን እሳዛኝ ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ማየትም ቁጭት ውስጥ ይከታል::
እናቶቻችና እህትቻችን በሚገባ የሚገለገሉበትን የእመቤታችን የእመ ቅዱሳን የቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተክርስቲያን ለመገንባት አሁን መሰረት ተጥሏል:: ይህንን ቤተመቅደስ በአጭር ጊዜ ገንብተን የአበው መነኮሳትን ድካም መቀነስ ይገባናል:: ከእመቤታችን የምናገኘው በረከትና ረድኤት ብዙ ነውና ሁላችንም ከበረከቱ በመሳተፍ ስማችንን በወርቅ እምድ እናጽፍ::
አባቶችችን ታሪክ ሠርተውልንና ለዘመናት የሚነገርለትን ድንቅ ቅርስ አስቀምጠውልን አልፈዋል:: እኛ አዲስ ታሪክ መጻፍ ባንችል እንኳን እነርሱ የሠሩትን ግማሹን ደግመን በመሥራት ልንመስላቸው ይገባናል:: ለጣና ሀይቅ ተጨማሪ ሞገስ እንጨምርለት::
ድጋፍ ለማድረግ:
ንግድ ባንክ: 1000731553134
ስልክ: -
0918240454
0906632367
0921612653
Tiktok: https://www.tiktok.com/@us...
Website: www.abuneyasay.com
Online Donation link: https://chapa.link/donatio...
2 months ago