Logo
Getu Temesgen
🚨 1,900 መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ ቆመዋል
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል። ከየካቲት 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት ተከትሎ የባህር ላይ ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቆሟል።

ወደ 1,900 የሚጠጉ የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እና በፋርስ ባህረ ሰላጤ አካባቢ መንቀሳቀስ አቅቷቸው ቆመዋል።

ኢራን "ከጥቃት አድራሾቹ አገራት ጋር ንክኪ ያላቸው መርከቦች በወሳኙ የሆርሙዝ ሰርጥ እንዳያልፉ" መከልከሏ ለቀውሱ ዋነኛ መንስኤ ሆኗል።

እንቅስቃሴያቸው ከተገታው መርከቦች መካከል ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ፣ የኬሚካል እና የተለያዩ የንግድ ዕቃዎችን የያዙ መርከቦች ይገኙበታል።

ይህ እገዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንር ከማድረጉም በላይ፣ ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት (Supply Chain) ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል እየፈጠረ ይገኛል። ሁኔታው ካልረገበ የዓለም ኢኮኖሚ የከፋ ጉዳት ሊገጥመው እንደሚችል ስጋቶች እየጨመሩ ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #middleeastcrisis #globaltrade #oilprice #hormuzstrait #breakingnews #shippingindustry #internationalrelations #energysecurity

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.