Logo
Getu Temesgen
የምስራች ለባለባጃጆች
አብሪ ሞተርስ የነዳጅ ባጃጆችን ወደ ኤሌክትሪክ ሊቀይር ነው!
#ethiopia | ​የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣትና በመገጣጠም የሚታወቀው አብሪ ሞተርስ (Abri Motors)፣ በሀገራችን ያሉ የነዳጅ ተጠቃሚ ባጃጆችን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር የሚያስችል ታሪካዊ ስምምነት ከቻይናው Jingshan Mining and Supply Chain Technology PLC ጋር ተፈራርሟል።

​አንዲት የነዳጅ ባጃጅ በወር እስከ 24 ሺህ ብር ለነዳጅ የምታወጣውን ወጪ፣ ወደ ኤሌክትሪክ በመቀየር ወደ 10 ሺህ ብር ዝቅ ለማድረግ ታቅዷል።

ባለባጃጆች የኤሌክትሪክ ባትሪውን በመግዛት ወይም በኪራይ መጠቀም ይችላሉ።

​ባትሪ ለመሙላት የሚባክነውን 4 ሰዓት ለማስቀረት፣ አንዱን ባትሪ ተጠቅመው ሲጨርሱ ሌላ ተሞልቶ የተዘጋጀ ባትሪ የሚቀይሩበት (Battery Swapping) አሠራር ተመቻችቷል።

የመንግሥትን የነዳጅ ጥገኝነት የመቀነስና የ"ግሪን ሌጋሲ" (Green Legacy) መርሐ ግብርን ዳር ለማድረስ ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

​አብሪ ሞተርስ የነዳጅ መኪናዎችን ወደ ኤሌክትሪክ በመቀየር፣ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በማቅረብና ምቹ የብድር አገልግሎቶችን በማመቻቸት የሚታወቅ ሀገር በቀል ድርጅት ነው።

​#getu #abrimotors #electricbajaj #greenenergy #ethiopia #transportation #techinnovation #sustainabletransport #addisababa #fueltoelectric #አብሪሞተርስ #የኤሌክትሪክባጃጅ #ቴክኖሎጂ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.