9 ስደተኞች በጅቡቲ የባህርዳርቻ ሞቱ
#ethiopia | በጁቡቲ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ከትናንት በስተያ የሰመጠች ጀልባ ውስጥ ከነበሩት ስደተኞች ዘጠኙ መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
ሌሎች 45 ስደተኞች ደግሞ በህይወት ይኑሩ ይሙቱ እንደማይታወቅ ድርጅቱ ገልጿል።
አደጋው የደረሰው ከትናንት በስተያ መጋቢት 15/ 2018 ዓ.ም. ለሊት ጅቡቲ ከምትገኘው ኦቦክ ከተባለችው ትንሽ ከተማ በስተሰሜን ባለ የባህር ዳርቻ መሆኑን IOM አስታውቋል።
ጀልባዋ 320 ሰዎችን አሳፍራ ነበር።
በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ መሠረት የምሥራቅ መስመር በሚባለው በዚህ የፍልሰት መንገድ ከሚሰደዱት አብዛኛዎቹ ከኢትዮጵያ የሚመጡ ናቸው።
በዚህ መስመር እ.ኤ.አ 2024 የ922 ስደተኞች ሕይወት አልፏል። ይህም እስከዛሬ ከተመዘገበው ሞት ከፍተኛው ተብሏል ያለው ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

4 months ago