#አብሪ ሞተርስ ነዳጅ ተጠቃሚ ባጃጅ ወደ ኤሌክትሪክ ባጃጆች ለመቀየር ስምምነት መፈረሙን አስታወቀ።
የኤሌክትሪክ መኪኖችን ከውጭ በማስመጣትና እዚሁ ሃገር ውስጥም በመገጣጠም ለደንበኞቹ በማቅረብ የሚታወቀውን አብሪ ሞተርስ ዛሬ ደግሞ የነዳጅ ተጠቃሚ ባጃጆች ወደ ኤሌክትሪክ ባጃጆች ለመቀየር የሚያስችል አብሮ የመስራት ስምምነት Jingshan mining and supply chain technology PLC ከተባለ የቻይና ኩባንያ መፈራረሙን ገልፀዋል።
ከቅርብ ግዝያት ወዲህ መንግስት የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ለማዳንና የነዳጅ ጥገኝነትን ለመቀነስ በሚል ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ማስገባት በስራ ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ወደ የኢሌክትሪክ መኪኖች እንዲቀይሩ መመርያ ማውረዱን የሚታወስ ነው።
ይህንን ትልቅ ሃገራዊ የመንግስት ውሳኔ ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየው አብሪ ሞተርስ በተለይ የግሪን ሌጋሲ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን አሁን ደግሞ በሃገራችን ያሉ ነዳጅ ተጠቃሚ ባጃጆች ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር በዘርፉ የበርካታት ዓመታት ልምድ ካለው ከJingshan mining and supply chain technology PLC ጋር ስምምነት ፈርመዋል።
የአብሪ ቢዝነስ ግሩፕ ዋና ስራ አስክያጅ (CEO) ወ/ሮ አብርሀት አየለ አንድ ባጃጅ በወር እስከ 24 ሺህ ብር ለነዳጅ እንደሚያወጣ ጥናቶች እንደሚያመላክቱ ገልፀው፡አብሪ ሞተርስ ደግሞ ይሄን ወጪ ከእጥፍ በላይ በመቀነስ ባለ ባጃጆች ወደ ኤሌክትሪክ እንዲቀይሩ ከተደረገ ብሁዋላ በወር 10 ሺህ ብር የነዳጅ ባትሪ በኪራይ አልያም ባትሪውን ገዝተው መጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተለይ በኪራይ የሚጠቀሙ ባለ ባጃጆች በቀን ሁለት ባትሪ እንዲጠቀሙ የተመቻቸ ሲሆን አንዱን ባትሪ ለመሙላት 4 ሰአት የሚፈጀው ግዜ ለስራ እንዲጠቀሙበት በማሰብ አንደኛውን ተጠቅመው ሲጨርሱ ሌላኛው ይሰጣቸዋል ሲሉ ደግሞ የJingshan mining and supply chain technology PLC ፕረዚደንት ዲንግ ዋን ዩ (Ding Wan You) ገልፀዋል ።
ይህ ደግሞ ባትሪ ለመሙላት የሚያጠፉትን ግዜ ሙሉ ግዝያቸውን በስራ ላይ እንዲያውሉ እንደሚያግዘ ነው ፕረዚደንቱ ጨምረው የገለፁት።
አብሪ ሞተርስ (Abri Motors) የነዳጅ መኪናዎን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀዩርበትን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርና በማስተዋወቅና አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በማስመጣት እንዲሁም በሃገር ውስጥ በመገጣጠም ለአከፋፈል ምቹ በሆነ የብድር አገልግሎት ጋር በማቅረብ የሚታወቅ ሃገር በቀል ድርጅት ነው።

2 months ago