ፊሊፒንስ ያለኝ የነዳጅ ክምችት ለ45 ቀናት ብቻ የሚሆን ነው አለች
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ፣ ፊሊፒንስ ከባድ የኃይል አቅርቦት ችግር ውስጥ መውደቋን አስታወቀች። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፈርዲናንድ ማርቆስ ሀገሪቱ የገጠማትን ስጋት ለመቆጣጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።
የፊሊፒንስ ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ሻሮን ጋሪ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የሚገኘው የነዳጅ ክምችት ለ45 ቀናት ብቻ የሚሆን ነው።
ፕሬዚዳንት ማርቆስ በነዳጅ አቅርቦት ላይ "የማይቀር አደጋ ገጥሞናል" ሲሉ ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት በነዳጅ፣ በምግብ እና በህክምና አቅርቦቶች ላይ ጥብቅ ክትትል የሚያደርግ ልዩ ኮሚቴ አቋቁሟል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መንግስት የተጠናከረ እርምጃዎችን በመውሰድ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት እንደሚያግዘው ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል።
ይህ የፊሊፒንስ ውሳኔ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው አለመረጋጋት በሩቅ ምስራቅ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫና ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #philippines #energycrisis #fuelshortage #ferdinandmarcos #globaleconomy #middleeastconflict #emergencydeclaration

3 months ago