Logo
SeledaPost
EBS 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ!

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በልባዊ ክብርና አክብሮት የተሞላ የምስጋና መልዕክቱን ለEBS ቴሌቭዥን።

ታላቁ ተስፈኛ እና ሰብአዊ ሰው አቶ አማን ፍስሃ ጽዮን በሕይወቱ ዘመን ለበጎ ሥራዎች ያለውን ድጋፍ በተግባር አሳይቶናል።

በተለይም መቄዶንያ  የሚሰራቸውን የበጎ አድራጎት ሥራዎች በEBS ቴሌቭዥን መድረክ ላይ ያለ ምንም ክፍያ እንዲቀርቡ በመፍቀድ ብዙ ሰዎች ድረስ እንዲደርሱ በማድረግና  በተለያየ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ አድርጎልናል ::

ይህም የልቡ ታላቅነትና የሰብአዊነት እውነተኛ ምልክት ነው።

እሱ ከዚህ ዓለም ድካም ካረፈ በኃላም  ለ40 ቀን መታሰቢያው በተደረገው ሰብአዊ ተግባር፣ ለ9,000 ተገልጋዮቻችን ቁርስ በማብላት የ ነፍስ ይማር ፕሮግራሙን ቤተሰቦቹ እና የEBS አባላት በመቄዶንያ አድርገዉ በደማቁ አስበውታል ::

የተደረገው ተግባር እጅግ የምንወደዉ እና የምናከብረዉ አቶ አማን ፍስሃ ፅዮንን እጅግ የሚያከብርና የማይረሳ ሰው መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ሥራ ነው።

በፕሮግራሙ ላይም በEBS ቴሌቭዥን ስም በባለቤቱ በ ወይዘሮ ማክዳ  1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር ድጋፍ ተበርክቶልናል።

ይህ ሁሉ የአማን ፍስሃ ጽዮን ራዕይና ልግስና እንደሚቀጥል ማሳያ ነው፤ ስሙም በበጎ አድራጎት እስከ ዘላለም ዘላቂ ሁኖ ይኖራል።

በመጨረሻም  ዶ/ር ብንያም  በ9,000 አረጋዉያን እና አዕምሮ ህሙማን ስም አመስግነዋል።

ይህ የተደረገው ታላቅ ድጋፍ በሁሉም ልብ ውስጥ ዘላቂ ምስጋና እንዲቀር አድርጎናል።

መቄዶንያ  በዚህ የተደረገውን ድጋፍ በከፍተኛ አክብሮት በመቀበል፣ ለቤተሰቡ መፅናናትን እንዲሁም ለነፍሱ መልካም ማረፊያን ይመኛል፤

ወይዘሮ ማክዳን እናመሰግናለን!

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.