Logo
FIDEL POST NEWS
​የኢራን የ3,000 ኪሎ ሜትሩ ድንገተኛ ሚሳይል ጥቃት

​ኢራን ከባህር ጠረፏ በ3,000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የዲዬጎ ጋርሺያ የአሜሪካና የእንግሊዝ የጋራ ጦር ሰፈር ላይ ያልተጠበቀ የሚሳይል ጥቃት ሙከራዋ አለምን አስገርሟል።

ምንም እንኳን ሁለቱ መካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ሚሳይሎች ኢላማቸውን ባይመቱም፣ የኢራንን ወታደራዊ አቅም አሳይቷል።

​የደህንነት ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ ጥቃት ኢራን ከዚህ ቀደም ራሷን ገድባበት የነበረውን የ2,000 ኪሎ ሜትር የርቀት ገደብ መጣሷን ያሳያል።

የደህንነት ባለሙያው ጄፍሪ ሉዊስ፣ የኢራን የጠፈር ምርምር ቴክኖሎጂ ለጦርነት ቢውል ከአህጉር አህጉር የመሻገር አቅም እንዳለውና የአውሮፓና የአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ከፍተኛ ስጋት ሊደቅን እንደሚችል ጠቁመዋል።

​ምንጮች :አናዶሉ የዜና ወኪል፣ አክሲዮስ፣ የአሜሪካ መከላከያ ደህንነት ኤጀንሲ


5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.