Logo
FIDEL POST NEWS
የአሜሪካ ሚኒስትሮች መኖሪያ ላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መታየታቸው የደህንነት ስጋት ፈጠረ

​በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት የሚኖሩበት ፎርት ማክኔር ወታደራዊ ካምፕ፣ ባልታወቁ ድሮኖች መታወኩ ተሰማ።

የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ድሮኖቹ በባለስልጣናቱ መኖሪያ ላይ ሲበሩ መታየታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ተፈጥሯል።

​ክስተቱ የተመዘገበው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የጀመሩትን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ ጥበቃው በከፍተኛ ሁኔታ ባለበት ወቅት ነው።

ድሮኖቹ በታዩበት ቅጽበት ሚኒስትሮቹን ከስፍራው ለማስወጣት ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ በመጨረሻ ግን በመኖሪያቸው እንዲቆዩ ተደርጓል።

ፔንታጎን ለደህንነት ሲባል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.